Articles

ታላቅ የተሳትፎ ጥሪ!

Print
Category: multi-news
Published Date Written by Super User

ታላቅ የተሳትፎ ጥሪ!

የአማራ አቀፍ ልማት ማህበር (አልማ) በበጐ አድራጐት ማህበራትና ድርጅቶች ማቋቋሚያ አዋጅ መሠረት በ1984 ዓ/ም የተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነ አገር በቀል ድርጅት ሲሆን፣በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት በግልጽ እንደተቀመጠው የማህበሩ ዋና ዓላማ የራስን/የህዝቡን የልማት ፍላጎት በራስ አቅም እውን የማድረግ አስተሳሰብና ተግባራዊ እንቅስቃሴን ለማጎልበትና ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ማህበሩ የክልሉን ሕዝብና መንግስት የልማት እንቅስቃሴ በተደራጀ ሕዝባዊ ተሳትፎና ንቅናቄ ስርዓት ባለው መንገድ ለመደገፍ ያስችለው ዘንድ የሚከተሉት ዝርዝር ዓላማዎች አሉት፡፡ እነሱም፡-

የአማራ አቀፍ ልማት ማህበር (አልማ) በበጐ አድራጐት ማህበራትና ድርጅቶች ማቋቋሚያ አዋጅ መሠረት በ1984 ዓ/ም የተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነ አገር በቀል ድርጅት ሲሆን፣በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት በግልጽ እንደተቀመጠው የማህበሩ ዋና ዓላማ የራስን/የህዝቡን የልማት ፍላጎት በራስ አቅም እውን የማድረግ አስተሳሰብና ተግባራዊ እንቅስቃሴን ለማጎልበትና ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ማህበሩ የክልሉን ሕዝብና መንግስት የልማት እንቅስቃሴ በተደራጀ ሕዝባዊ ተሳትፎና ንቅናቄ ስርዓት ባለው መንገድ ለመደገፍ ያስችለው ዘንድ የሚከተሉት ዝርዝር ዓላማዎች አሉት፡፡ እነሱም፡-

  • የአማራ ክልል ሕዝብ የበለፀገና አስተማማኝ የኑሮ ደረጃ እንዲኖረው የሚያስችሉ የትምህርት፣የጤና የመሠረታዊ ክህሎት ስልጠናና የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሌሎችም የልማት መስኮች እንዲስፋፉ መደገፍ፣
  • የአማራ ክልል ሕዝብ የኑሮ ደረጃ እንዲሻሻል ጥረት ከሚያደርጉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በትብብር መስራት፣
  • ባለኃብቶች፣ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ለክልሉ ማህበራዊ ልማት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትና ድጋፍ እንዲያበረክቱ ማስተባበርና መደገፍ፣
  • በክልሉ ህብረተሰብ አቀፍ የአካባቢ እንክብካቤና ጥበቃ ስራዎች እንዲስፋፉ ማስተባበርና ድጋፍ ማድረግ፣   

በዚሁም መሠረት ማህበሩ የሚከተሉትን ራዕይ፣ተልዕኮና ዕሴት ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡

ራዕይ

በ2017 የክልሉ ሕዝብ ፍጹም በሆነ ልማታዊ አንድነት የራሱን የልማት ችግሮች በራሱ አቅም በብቃት የሚፈታ ማህበረሰብ ሆኖ ማየት፣

ተልዕኮ

የክልሉን ሕዝብና የልማት ደጋፊዎች በዘላቂነት በማንቀሳቀስ በትምህርት፣ በጤናና የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ በክልሉ ሕዝብ የማህበራዊ የልማት ተጠቃሚነት አስተዋጽኦ ማድረግ፣

 

ዕሴቶች

ግልጸኝነትና ተጠያቂነት

ታማኝነት

ባለቤትነትና ተነሳሽነት

ቁጠባና ውጤታማነት

የሕዝብ ተጠቃሚነት

ከአድሎዊና ከኪራይ ሰብሳቢነት የነፃ ድጋፍ

አዳዲስ አሰራርን መጠቀም

አጋርነት

ዘላቂነት

እነኝህን መሠረት በማድረግ ማህበሩ በሕዝቡ ተሳትፎ በርካታ የማህበራዊ አገልግሎት ድጋፎችን ሲያደርግ የቆየ ሲሆን፣ በቀጣይ ዓመታትም በላቀ የሕዝብ ተሳትፎ የላቀ ልማታዊ ድጋፍ ለክልሉ በማበርከት ክልሉ ጠንካራ ክልል ይሆን ዘንድ የለውጥ ዕቅድ በመንደፍ ወደ ተግባር ለመሸጋገር በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

በቀጣይ ዓመታት በለውጥ ዕቅዱ ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮችና ግብም፡-

  • የአልማን አቅም በመገንባትና ከማንኛውም አግላይ አመለካከት በፀዳ መልኩ መልዓተ ሕዝቡን በማሳተፍ የክልሉን ሕዝብ የልማት ተሳታፊና ተጠቃሚ ማድረግ፣
  • የክልሉን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማሻሻል ልዩ ፕሮግራም በማካሄድ  በአሁኑ ወቅት በስታንዳርዱ መሠረት የክልሉ የትምህርት ደረጃ ከሚገኝበት 16% ወደ 50% ማሳደግ፣
  • ማህበሩ ለሚያከናውናቸው ማህበራዊ አገልግሎቶች አስተማማኝ የገቢ ምንጭ እንዲኖረው ማድረግ፣
  • በአልማ ዙሪያ የሚሰባሰበው ሕዝብ ራሱንና ክልሉን ይጠቅም ዘንድ በክልሉ ልማት ተሳታፊ እንዲሆን ሁኔታዎችን ማመቻቸት፡፡
  • ከላይ ከተቀመጡ ጉዳዮችና ግቦች ጋር በማስተሳሰርና አግባባ ያላቸውን አካላት በማሳተፍ በአስር ሽዎች ለሚቆጠሩ ወጣቶች የሙያ ስልጠናና የሥራ ዕድል እንዲያገኙ ማድረግ ነው፡፡

በአጠቃላይ ከማንኛውም አግላይ አመለካከት በፀዳ መልኩ የክልሉን ሕዝብና በክልሉ ልማትና ዕድገት በጐ አመለካከት ያላቸውን ኢትዮጵያዊያን በማሰባሰብ፤ የክልሉን ልማት ለማፋጠንና ልማታዊ ሕዝብና አንድነት ለማምጣት ማህበራችን ተዘጋጅቷል፡፡

በመሆኑም ከላይ የተዘረዘሩትን ጉዳዮች የሚያመላክት የማህበሩን ሎጐ እና መሪ ቃል በሕዝብ ተሳትፎ ማዘጋጀት በማስፈለጉ ይህ ሕዝባዊ ጥሪ ቀርቦልዎታ፡፡

ስለሆነም ሊሆን ይገባል ብለው የሚያስቡትን ሎጐና መሪ ቃል (ከነማብራሪያው) በአካል ወይም በማህበራችንና በአማራ ማስ ሚዲያ ድህረ ገጽና የፌስቡክ አድራሻ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ትልኩልን ዘንድ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

የአማራ አቀፍ ልማት ማህበር (አልማ)

Amaha Development Association (ADA)

          አድራሻ

                                ባህርዳር

                   ስልክ    251 58 220 10 08

                           251 58 226 67 73

                           251 58 226 63 65

                   ፋክስ    251 58 220 10 88

                   e-mail:  ada.hq@ethionet.net.et

                     Website:-  http://www.ada.org.et

                                          ፖስታ  307

                   አዲስ አበባ

                    ስልክ   251 11 551 78 86

                    ፋክስ   251 11 551 77 95

                      ፖስታ 13685

                       e-mail፡ada.liaison@ethionet.et

               አማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት

                       ስልክ  251 58 320 72 07

                       e-mail:  This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

                         Website:-   http://www.amharaweb.com


Copyright © 2012  ADA, All Rights Reserved.               Designed & Developed by :Yibeltal Ferede