Vacancy

የአማራ  ልማት ማህበር /አልማ/ ለዋናው ጽ/ቤት ከዚህ በታች በተገለፁጽ ክፍት የስራ መደቦች ከማህበሩ ሠራተኞች መካከል በዝውውር እና ደረጃ ዕድገት አወዳድሮ መመደብ ይፈልጋል፡፡

የሥራ ዝርዝር

የሥራ መደቡ መጠሪያ ዌብ ዲዛይነር (የዲዛይን፣ ግራፊክስና ኅትመት ባለሙያ)

የቅርብ ኃላፊ            የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

የሥራ ሂደት             የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት

ቡድን                  …………………………….

ዋና ዋና ተግባራት

የልማት ማህበሩ በሚያዘጋጃቸው የኤሌክትሮኒክስና ህትመት ሚዲያዎች ፈጠራ በታከለበት መንገድ ዲዛይናቸውንና ሌይ አውት ማከናወን፤ በማህበሩ የሚዘጋጁ ዓመታዊና ልዩ መፅሄቶች፣ በራሪ ወረቀቶች፣ ቢልቦርድ ላይ የሚፃፉ መልዕክቶችና ፎቶ ግራፎችን፣ ቻርቶችን፣ የዕውነታ ዝርዝሮች ለባለድርሻ አካላት ሳቢ በሆነ መንገድ ዲዛይን ማዘጋጀት፤ ትክክለኛ እና ወቅታዊነት ያላቸውን የፎቶ ግራፍም ሆነ የቴክስት መረጃዎችን በማህበሩ ዌብ ሳይት፣ ፌስ ቡክ ቲውተር፣ ዩቲዩብ፣ ሊንክደንና በመሳሰሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች መጫን፡፡

ዝርዝር ተግባራት

 1. የልማት ማህበሩ ለባለድርሻ አካላት በሚያዘጋጃቸው በአጠቃላይ የኤሌክትሮኒክስም ሆነ  ህትመት ሚዲያዎች (በሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣ በጋዜጣ፣ በመፅሄት፣ በጆርናል፣ ኮርፖሬት ሪፖርቶችንና ሌሎችንም ወዘተ…ፈጠራ በታከለበት መንገድ ዲዛይናቸውንና ሌይ አውት ሥራ ያከናውናል፤ 
 2. በማህበሩ የሚዘጋጁ ዓመታዊና ልዩ መፅሄቶች፤ በራሪ ወረቀቶች፣ ቢልቦርድ ላይ የሚፃፉ መልዕክቶችና ፎቶ ግራፎችን፣ ቻርቶችን፣ የዕውነታ ዝርዝሮች ለባለድርሻ አካላት ሳቢ በሆነ መንገድ ዲዛይናቸውን ያዘጋጃል፤
 3. የማህበሩን ዌብ ሳይት ዲዛይን ሳቢ በሆነ መንገድ ያዘጋጃል፣
 4. ትክክለኛ እና ወቅታዊነት ያላቸውን የፎቶ ግራፍም ሆነ የቴክስት መረጃዎችን በማህበሩ ዌብ ሳይት፣ ፌስ ቡክ ቲውተር፣ ዩቲዩብ፣ ሊንክደንና በመሳሰሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች ያሰራጫል፣ ይጭናል፤
 5. በክፍሉ የሚዘጋጁ የሬዲዮ፣ የቴሌቭዥን እና የጋዜጣ ፕሮግራሞች አርቲክሎች፣ ዶክመንተሪዎች፣ስፖርቶች/ማስታወቂያዎች ዲዛይንና ሌይአውት ይሰራል፤የመልዕክታቸውን ዓይነት ቀለም፣ ፎቶግራፎችንና ስዕሎችን ማብራሪያዎችን ያከናውናል፤
 6. ስለ ማህበሩ በልዩ ልዩ የውጭም ሆነ የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች የሚለቀቁ አዎንታዊም ይሁኑ አሉታዊ የቪዲዮ፤ የኦዲዮ እና የቴክስት መልዕክቶችን ሞኒተር ያደርጋል፣ ከአስተያየት ጋር ለቅርብ የሥራ ኃላፊው ያቀርባል፣ ከማህበሩ ዌብ ሳይት ሊንክ መደረግ ያለባቸውን ለክፍሉ አቅርቦ ያስወስናል፤
 7. በልዩ ልዩ መድረኮች ተገኝቶ የማህበሩን ስራዎች ፕሮሞሽናል ዲስፕሌይ ያቀርባል፤
 8. የማህበሩ ሎጎ እንዲሻሻል ይጥራል፤
 9. በተጨማሪም ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጠውን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራት ያከናውናል፡፡

ተፈላጊ የትምህርት ደረጃና የሥራ ልምድ

ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፡- ከታወቀ ዩኒቨርስቲ በመጀመሪያ ዲግሪ

ሲኒማቶግራፊክስ፣ኮምፒውተር ሳይንስ፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ኮምፑተር ኢንጅነሪንግ፣ ኮምንኬሽን ኤሌክትሮኒክስ/ፎቶ ኢሜጅንግ ወርከረስ፣ አርት ፔይንቲንግ፣ ኦዲዮ ቪዲዮ ቴክኖሎጅ፣ኦዲዮ ቪዲዮ ኢኩፕመንት፣እና ተዛማች ዲፓርትመንቶች የመጀመሪያ ዲግሪና 3 ዓመት በሙያው የሥራ ልምድ ያለው/ያላት

ወይም ከታወቀ ኮሌጅ/ቴክኒክና ሙያ ት/ቤት በህትመት ቴክኖሎጂ/ ዲዛይንና ግራፊክስ ሙያ (10+3) ወይም ደረጃ IV ዲፕሎማና በሙያው የ7 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ያላት፤

ወይም  ከታወቀ ኮሌጅ/የቴክኒክና ሙያ ት/ቤት በዲዛይንና ግራፊክስ ሙያ (10+2) ወይም ደረጃ III ሠርተፊኬትና በሙያው የ9 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ያላት

ወይም ከታወቀ ኮሌጅ/የቴክኒክና ሙያ ት/ቤት በዲዛይንና ግራፊክስ ሙያ (10+1) ወይም ደረጃ II ሠርተፊኬትና በሙያው የ11 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ያላት

 • Ø ደመወዝ፡---------------------------------------------------------- 8440.00
 • Ø ደረጃ-------------------------------------------------------------9
 • የስራ ቦታ፡- ------------------------------------------- ዋናው መስሪያ ቤት ባህር ዳር
 • ጾታ፡------------------------------------------------------------------ አይለይም
 • ብዛት------------------------------------------------------- 01

የምዝገባ ጊዜና ቦታ፡- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሆን ለዋናው መስሪያ ቤት ሰራተኛች ቢሮ ቁጥር 104 በመቅረብ መመዝገብ የሚቻል እና ለአዲስ አበባ፤ለዞንና ወረዳ ተወዳዳሪዎች በማስተባበሪያና ዞን ጽ/ቤቶች መሆኑን እናስታውቃለን፡፡


Copyright © 2012  ADA, All Rights Reserved.               Designed & Developed by :Yibeltal Ferede