Membership Development Program

የአባላት ልማት ፕሮግራም በ5 አመት (ከ2009- 2013 ዓ.ም) የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

የማህበሩ ዋናዉ መሰረት አባላትና የክልሉ ህዝብ ነዉ፡፡ እንዲሁም ከክልሉ ውጭ ያሉ የማህበሩ በጎአድራጊ አባላትና ደጋፊዎች ናቸው፡፡ አልማ ይህንን ዋነኛ አቅም በተደራጀ መልኩ ለመጠቀም ባለፉት ማለትም ከ2004- 2008 ዓ.ም ድረስ ባሉት 5 አመታት በማህበሩ ስትራቴጅክ እቅድ መሰረት የማህበሩን ህዝባዊ መሰረት በማስፋት የክልሉን ህዝብ ማህበራዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ አሰተዋፅኦ አድርጓል፡፡ ለዚህም የማህበሩን ህዝባዊ መሰረት ለማስፋት በተሰራው ስራ የማህበሩን አባላት ቁጥር በስትራቴጂው እቅድ መነሻ 2003 በጀት አመት ከነበረበት 1.2 ሚሊዮን ወደ5,042,211 ለማድረስ ታቅዶ በስትራቴጂክ እቅዱ መጨረሻ 2008 በጀት አመት የእቀዱን 2,905,506 (81.42%) በማከናወን አጠቃላይ የማህበሩን አባል ቁጥር 4,105,506 ማድረስ ተችሏል፡፡

ከማህበሩ አባለት መደበኛ መዋጮና ደጋፊዎች በአንድ በጀት አመት ለልማት ይሰባሰብ የነበረውን ሃብት በ2003 በጀት አመት ከነበረበት ብር12,085,080 በ2008 በጀት አመት ብር 250 ሚሊዮን በላይ በአመት የመሰብሰብ አቅምን በማጎልበት በአጠቃላይ በ5 አመት (ከ2004- 2008 ዓ.ም) ብር737,059,657 ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 778,133,329 (105.57%) በመሰብሰብ ለልማት እንዲውል ተደርጓል፡፡ በመደረግ ላይም ነው፡፡

በቀጣይም ይህን ስኬት ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ከ2009 በጀት አመት ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ በሚገኘው የማህበሩ የ5 አመት ስትራቴጅክ እቅድ ላይ ለትም/ት፣ ለጤና እና ለስራ እድል ፈጠራ የልማት ዘርፎች ትኩረት በማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡ በተለይም ለትም/ት ጥራት መረጋገጥ ለቅድመ መደበኛ ትም/ት ድጋፍ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በመንቀሳሰቅስ ላይ ነው፡፡

የአልማን ህዝባዊ መሰረትና የልማት ፋይናንስ  በላቀ ደረጃ በተከታታይ አመታት ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል፡፡ የማህበሩ የልማት ድጋፍ ዋነኛ የሀብት ምንጭም የማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች /ህዝቡ/ እንዲሆን የማድረግ  መሰረታዊ አቅጣጫ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየተሰራ ነው፡፡ በቀጣይም በተጠናከረ መልኩ ይሰራል፡፡

 በቀጣይ አምስት አመት (ከ2009- 2013 ዓ.ም) የአባላትልማት ፕሮግራም የሚከተለው አጠቃላይ አላማ አለው

 • የማህበሩ የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት  አስተሳሰብና ተግባር እንዲጎለብት በማድርግ የማህበሩን  ሕዝባዊ መሰረት በማስፋትና የፋይናንስ አቅሙን በማሳደግ ቀጣይነት ያለዉ የልማት ድጋፉን ለማረጋገጥ የሚያስችል አስተማማኝ የገቢ መሰረት እንዲኖረዉ ማድረግ ነው፡፡

በቀጣይ አምስት አመት (ከ2009- 2013 ዓ.ም) ዋና ዋና ግቦች

ግብ 1:   ጠቅላላ የማህበሩን አባላት ቁጥር በ2008 በጀት አመት ከነበረበት 4,105,506

          ወደ 7,788,119 ማድረስ፣

ግብ 2:  ከማህበሩ አባላት የሚሰበሰብ እና ለልማት የሚውል ሃብት በ2008 በጀት አመት ከነበረበት

          ብር 778,133,329 ብር 1,819,727,486፣

 ግብ 3፡ ከአገር ውስጥ 402,500     ከውጭ አገር  750  በድምሩ 403,250  በጎ ፈቃደኞች በማፍራት

          ብር 50 ሚሊዮን የሚያወጣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማግኘት፣

ዋና ዋና ማስፈፀሚያ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎች

 • የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አስተሳሰብን በማስረፅ የማህበሩ አባላት፣ ደጋፊዎች፣ በየትኛውም አለም የሚገኙ በጎአድራጊዎች ባላቸዉ ዕዉቀት፣ ጉልበት፣ ገንዘብና ማቴሪያል የክልሉን  ህዝብ የሚያገለግሉበትን አሰራር የማጠናከር አቅጣጫ አጠናክሮ ማስቀጠል፣ 
 • የተለያዩ የህዝብ ሞብላይዜሽን ስራዎችን በታቀደ፣ በተደራጀና በተቀናጀ መንገድ በመጠቀም የአባላት ማፍራት እንቅስቃሴን በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተጠናክሮ ተግባራዊ የሚሆንበትን አቅጣጫ መከተል፣
 •    አሳታፊ የልማት ዕቅድ ዝግጅት አቅጣጫን መከተል፣ 
 •  የማህበሩን አባላትን ተሳትፎ እና ተነሳሽነት የሚያበረታቱ አሰራሮችን ማጠናከር፣ 
 • ግልጽነትንና ተጠያቂነትን ያረጋገጠ የልማት ሃብት/ ገንዘብ   አሰባሰብ ስርዓትን ማጠናከር፣
 •  በየደረጃዉ የሚካሄዱ የማህበሩ ጉባኤዎች በተለይም በቅርንጫፍ እና መሰረታዊ ማህበር ደረጃ የሚካሄዱ ጉባኤዎችን ተቋሟዊ አቅምን ለመገንባትና ለዕቅድ አፈፃፀምም ስኬታማነት ዋነኛ መሳሪያ አድርጎ የመጠቀምን አቅጣጫን መለከተል፡፡

 በፕሮግራሙ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

 • የማህበሩን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የማስፋፋት ስራ ማከናወን፣ የማደራጀትና ግንዛቤ ፈጠራ ስራን ማከናወን፣
 • የማህበሩን ህዝባዊ መሰረት ለማስፋት አዳዲስ አባላትን ማፍራትና ነባር አባላትን ማስቀጠል፣
 • ከአባላትና ደጋፊዎች ለልማት ማስፈፀሚያ ሃብት ማሰባሰብ፣
 • ለታቀዱ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ማፍስፋፊያና ድጋፍ ማስፈፀሚያ የሚሆን የልማት ሃብት ማስተላለፍ ወዘተ--- ናቸው፡፡

Copyright © 2012  ADA, All Rights Reserved.               Designed & Developed by :Yibeltal Ferede