አማራ ልማት ማህበር /አልማ/ ህዝባዊ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት አልማ 2012-2014 በሚል መሪ ቃል ማህበራዊ ችግሮቻችንን በራስ አቅም ለመፍታት የሚያስችል ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሮልናል ሲሉ የአንዳበት ከተማ ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡ ነዋሪዎቹ ይህምን ያሉት 08/06/2012 ዓ.ም በአንዳቤት ከተማ ባካሄዱት የልማት ሀብት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ነው፡፡

በእለቱም የተለያዩ የሀይማኖት አባቶች ፤ ባለሀብቶች፤ የአነስተኛና ጥቃቅን አንቀሳቃሾች፤ የከተማ ነዋሪዎች፤ የመንግስት ሰራተኞች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዩች የተገኙ ሲሆን ወረዳው ለሚያከናውነው የት/ቤቶች ደረጃ ማሻሻያ ፕሮጀክት የሚውል በአይነት ፣በማቴሪያል እና ቃልየተገባ ብርን ጨምሮ 745ሺ339 ብር በላይ እንደሚያበረክቱ በመድረኩ አረጋግጠዋል፡፡

በመድረኩ ላይም ነዋሪዎቹ 87 ሺ 450 ብር እጅ በእጅ በእለቱ በአልማ ደረሰኝ ገቢ ያደረጉ ሲሆን ከ549ሺ ብር በላይ ቃል-ኪዳን የተገባ እንዲሁም በቁሳቁስ 119 ኩንታል ለግንባታ የሚውል ስሚንቶ፣የ84ሺ ብር አሽዋ፣ የ9ሺ ብር የግንባታ ድንጋይ እና ጤፍ በማቅረብ በአንዳቤት ወረዳ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሳግ የትምህርትን ጥራት ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ በቁርጠኝነት ተናግረዋል ፡፡

የአንዳቤት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ መርሻ በበኩላቸው አንዳቤት ወረዳ ህዝብ የራሱን ችግር በራሱ አቅም ለመፍታት አልማ ያቀደውን እቅድ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም እና የወረዳው ህዝብ ከዚህ በፊት ለልማት ያለውን ተነሳሽነት በማጠናከር በ2012 ዓ.ም 40 ሚሊዮን ብር የታቀደ ቢሆንም ከዚህ በላይ የልማት ሀብት በማሰባሰብ ግንባር ቀደም እንደሚሆኑ ገልጸው በተለያዩ ቀበሌዎች ቃል የተገባ የልማት ሀብት እስከ የካቲት 30/2012ዓ.ም ማጠናቀቅ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ዋና አስተዳዳሪው አክለውም የአንዳቤት ከተማ ነዋሪዎች በዛሬው መድረክ ያሳዩትን መነሳሳት አጠናክረው በመቀጠል የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሳደግ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ማፍራት እንደሚገባ ገልጸው በቀጣይም የአልማን እቅድ በመደገፍ በማህበራዊ ዘርፍ ያሉብንን ችግሮች በተባበረ ክንድ መፍታት ይገባል ካሉ በኋላ የወረዳው ተወላጅ የሆኑ በክልሉ ውስጥም ሆነ ከክልሉ ውጭ የሚገኙ ባለሀብቶች ለወረዳው ልማት እረቀት ሳይገድባቸው ያበረከቱትን አስተዋጽኦ በመጥቀስ በወረዳው ህዝብ ስም አመስግነዋል፡፡

አማራ ልማት ማህበር /አልማ/ ህዝባዊ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት አልማ 2012-2014 በሚል መሪ ቃል ማህበራዊ ችግሮቻችንን በራስ አቅም ለመፍታት የሚያስችል ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሮልናል ሲሉ የአንዳበት ከተማ ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡ ነዋሪዎቹ ይህምን ያሉት 08/06/2012 ዓ.ም በአንዳቤት ከተማ ባካሄዱት የልማት ሀብት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ነው፡፡

በእለቱም የተለያዩ የሀይማኖት አባቶች ፤ ባለሀብቶች፤ የአነስተኛና ጥቃቅን አንቀሳቃሾች፤ የከተማ ነዋሪዎች፤ የመንግስት ሰራተኞች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዩች የተገኙ ሲሆን ወረዳው ለሚያከናውነው የት/ቤቶች ደረጃ ማሻሻያ ፕሮጀክት የሚውል በአይነት ፣በማቴሪያል እና ቃልየተገባ ብርን ጨምሮ 745ሺ339 ብር በላይ እንደሚያበረክቱ በመድረኩ አረጋግጠዋል፡፡

በመድረኩ ላይም ነዋሪዎቹ 87 ሺ 450 ብር እጅ በእጅ በእለቱ በአልማ ደረሰኝ ገቢ ያደረጉ ሲሆን ከ549ሺ ብር በላይ ቃል-ኪዳን የተገባ እንዲሁም በቁሳቁስ 119 ኩንታል ለግንባታ የሚውል ስሚንቶ፣የ84ሺ ብር አሽዋ፣ የ9ሺ ብር የግንባታ ድንጋይ እና ጤፍ በማቅረብ በአንዳቤት ወረዳ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሳግ የትምህርትን ጥራት ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ በቁርጠኝነት ተናግረዋል ፡፡

የአንዳቤት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ መርሻ በበኩላቸው አንዳቤት ወረዳ ህዝብ የራሱን ችግር በራሱ አቅም ለመፍታት አልማ ያቀደውን እቅድ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም እና የወረዳው ህዝብ ከዚህ በፊት ለልማት ያለውን ተነሳሽነት በማጠናከር በ2012 ዓ.ም 40 ሚሊዮን ብር የታቀደ ቢሆንም ከዚህ በላይ የልማት ሀብት በማሰባሰብ ግንባር ቀደም እንደሚሆኑ ገልጸው በተለያዩ ቀበሌዎች ቃል የተገባ የልማት ሀብት እስከ የካቲት 30/2012ዓ.ም ማጠናቀቅ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ዋና አስተዳዳሪው አክለውም የአንዳቤት ከተማ ነዋሪዎች በዛሬው መድረክ ያሳዩትን መነሳሳት አጠናክረው በመቀጠል የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሳደግ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ማፍራት እንደሚገባ ገልጸው በቀጣይም የአልማን እቅድ በመደገፍ በማህበራዊ ዘርፍ ያሉብንን ችግሮች በተባበረ ክንድ መፍታት ይገባል ካሉ በኋላ የወረዳው ተወላጅ የሆኑ በክልሉ ውስጥም ሆነ ከክልሉ ውጭ የሚገኙ ባለሀብቶች ለወረዳው ልማት እረቀት ሳይገድባቸው ያበረከቱትን አስተዋጽኦ በመጥቀስ በወረዳው ህዝብ ስም አመስግነዋል፡፡

ሰሜን ወሎና አካባቢው አልማ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ስትራቴጃያዊ የለውጥ ዕቅዱን በህዝብ ንቅናቄ እየፈፀመ ነው፡፡ ማስተባበሪያ ፅ/ቤቱ ሞዴል ቀበሌዎችን ቅድሚያ ሰጥቶ የልማት ሀብት በመሰብሰብና አባል በማፍራት የተገኘውን ተሞክሮ ወደ ሌሎች አካባቢዎች በማስፋት የማህበራችን ተቋማዊ አቅም በሚገነባ መንገድ እያፈጸመ ይገኛል፡፡

ማስተባበሪያ ፅ/ቤቱ ህዘውባዊ ንቅናቄ መድረኩን ወደ ሌሎች ካሰፋባቸው ቀበሌዎች መካከል ግዳን ወረዳ የምትገኘው የመሮራ ቀበሌ የካቲት 06/07/2012 ዓ.ም የተካሄደው የልማት ሀብት ማሰባሰቢያ መድረክ ነው፡፡

ማስተባበሪያ ፅ/ቤቱ በቀበሌው የሚታየውን የትምህርት ተቋም ማሳደግ ሁነኛ ችግር መሆኑን  ህፃናት ከ8ኛ ክፍል በኋላ ለመቀጠል እየደረሰባቸው የሚገኘውን ተጨባጭ ችግር ለነዋሪዎች ማስገንዘብና ለመፍትሄው መግባባትና መተማመን መድረስ ዋና ተግባር አድርጎ አስቀድሞ ፈፅሞታል፡፡

ይህ በአካባቢው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ችግር መለየትና ለመፍትሄው  መግባባት ለመድረስ የወረዳና ቀበሌ አመራሮች ግንባር ቀደም ሚና እንዲጫወቱና የልማት ሀብት እንዲወስኑ ማድረግ ተጭሏል፡፡ የአካባቢው ተፅኖ ፈጣሪና ዕምነት የሚጣልባቸው የቀበሌ ኮሚቴዎችን ወደ ስራ ማስገባት ተችሏል፡፡ የሀይማኖት አባቶች ለመፍትሄው ዙሪያ ምዕመናን እንዲቀሰቅሱ ተደርጓል፡፡ በአጠቃላይ በልማት ሀብት ማሰባሰቢያ መድረኩ ልዩ ልዩ የሀብት ማሰባሰቢያ ዘዴዎች ተግባር ላይ የዋሉ ሲሆን በዕለቱ  105 ሺ 750 ብር በጥሬ ገንዘብ መሰብሰብ   246 ሺ 900 ብር እስከ የካቲት 20 ቀን ገቢ ለማድረግ በዓይነትና በገንዘብ ቃል ተገብቷል፡፡

የልማት ሀብት ማሰባሰቢያ መድረክ የትምህርት ቤቱ ለሚገነባበት ቦታ ከአንድ አርሶ አደር በነፃ የተበረከተ ሲሆን የግንባታው የመሰረት ድንጋይም በዕለቱ ተቀምጧል፡፡ በአጠቃላይ ከወረዳ እስከ ቀበሌ የሚገኘው የመንግስት ፤አልማና ነዋሪው ህብረተሰብ በቅንጅት በራስ አቅም መልማት ብቻ ሳይሆን የዘላቂ ልማት ተምሳሌ መሆኑን  አስመስክሯል፡፡

አቶ ጌቴ ሙላት ጀምበሬ

አባላት ልማት ዳይሬክተር

ሙሉ የማስፋት መጣጥፉን በዌብ ሳይታችን አርቲክል ገፅ ይመልከቱ፡፡ 

የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) የገቢ ማስገኛ ተቋማት ልማት ዳይሬክተር ዮሐንስ ታረቀኝ እንደገለጹት የክልሉን የልማት ሥራዎች ቀጣይነት ለማረጋገጥ በቀጣይ ዓመታት ቋሚ የገቢ ማስገኛ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ይሠራል፡፡

ማኅበሩ በክልሉ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን ከአባላቱ እና ከለጋሽ ድርጅቶች በሚሰበስበው ሀብት እያከናወነ እንደሚገኝ የገለጹት ዳይሬክተሩ የክልሉን ልማት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ከአባላቱ እና ለጋሽ ድርጅቶች ገቢ በተጨማሪ ቋሚ የሀብት ማስገኛ ፕሮጀክቶን ለማቋቋም ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል፡፡

ዳይሬክተሩ እንደገለጹት የመድኃኒት ፋብሪካ፣ የእንግዳ ማረፊያና ሁለገብ ሕንጻዎች፣ የሴቶች ንጽሕና መጠበቂያና የሕጻናት የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች በአዲስ ይገነባሉ፤ የዋንዛየ ፍል ውኃ እና የጢስ ዓባይ ‹ስፕሪንግ› ውኃ ፋብሪካዎች ደግሞ ማስፋፊያ ይደረግላቸዋል፡፡ የማስፋፊያ ፕሮጀክቶን ሥራ የጀመረ ሲሆን አዳዲሶቹ ፕሮጀክቶች በዚህ ዓመት ጥናቶችን በማጠናቀቅ በሚቀጥለው ዓመት የግንባታ ሥራ እንደሚጀምር ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ ፕሮጀክቶቹ 267 ሚሊዮን 935 ሺህ 248 ብር እንደሚጨርሱም ዳይሬክተሩ አመልክተዋል፡፡

አልማ በቀጣይ ሦስት ዓመታት በሚያከናውነው ልማት 21 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ለማሰባሰብ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሆነ ተገልጧል፡፡ ገንዘቡም በአብዛኛው በክልሉ የሚታየውን አጠቃላይ የትምህርት ቤቶች ደረጃ ለማሻሻል ሥራ ይውላል፡፡ ቀሪው የልማት ሀብት ደግሞ ለዘላቂ ልማት ገቢ ማስገኛ ፕሮጀክቶች ግንባታ እንደሚውል ከማኅበሩ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡

Deal signed a tripartite agreement to develop Smart Green Villages in Gondar

Gondar, Smart Green Villages

History was made today in the house construction industry of Ethiopia as Smart Village Projects Limited signed a tripartite agreement with Amhara Development Association (ADA) and Mayor office of Gondar city for the construction of 130 household system in Gondar zoria district.

Advertise your company in Africa News channel Magazine and online website, African Best print and online media in the African union; This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ; +251941812783 (Ethiopia)

A Memorandum of Understanding has been signed a tripartite agreement with the three parties. The Memorandum of Understanding was signed by the Gondar Mayor’s Office between the Amhara Development Association (ADA), the Gondar Mayor’s Office and the subsidiary of smart village solution Company in the United States.

Communication Director of Amhara Developmnet Association Mr. Alemayehu Moges told to Africa News Channel an agreement with the Global smart village solution in America to develop Ethiopian villages into “smart green villages” with an aim to build communities’ resilience to climate change. The deal aimed at the delivery of reliable power supply to underserved economic clusters like markets, industries, plazas, estates, MSMEs etc across Gondar. Over 130 more sites has been identified and will be developed.

A village is one that is developed economically using natural resources in a sustainable manner, without affecting the environment.

Mr Alemayehu Moges, the Communication Director of ADA said that the modern village construction includes the agreement that the 130 homes will provide clean drinking water, solar energy, education, health and other infrastructure, while the technology, housing and infrastructure costs will be fully covered by the Smart Village Solutions Company.

This smart green village ideally targets at least 130 households.

Gondar District Dersgie Miriam Kebele Modern Village Construction Signature Agreement by ADA the Deputy Chief Executive Officers of the Association, Araga Tadesse and Hamid Ahmed, the Mayor of Gondar Berehuen Kassaw, and Solution Villa, signed by Steve Jones, President of Smart Living Global. Officials said that by incorporating the term “Smart” to the Green Village, it means that besides having environmentally-friendly amenities, they will incorporate appropriate ICT capabilities in the villages to ensure their connectivity.

“In the Smart Green Village, we will bring all sustainable principles including low carbon gas emissions, energy efficiency. At this stage we are bringing model houses that are affordable with components of raw materials that are sustainable and that can be sourced and manufactured locally,” he said.

The green village is located in a rural set-up with existing or potential activities in the field of agriculture in order to test the impact of sustainable energy use, connectivity, and smart mobility solutions.

The Mayor of Gondar, Berehuen, said the pilot project will be expanded to other parts of the Amhara region and in the country. “We think, if successful, we can export the solutions to the rest of the country. We have model houses we will use in those villages and close to a year, we will have something to present,” he added.

በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ሦስት ትምህርት ቤቶችን ለማስገንባት ቃል ገቡ።

በዋሽንግተን ዲሲ በተዘጋጀው የዳስ ትምህርት ቤቶችን ገጽታ መቀየሪያ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ከ 1ነጥብ 5 ሚሊዬን ብር በላይ ተሰብስቧል።

የዳስ ትምህርት ቤቶችን ገጽታ ለመቀየር በዋሽንግተን ዲሲ ዛሬ በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር የአማራ ተወላጅ ግለሰቦች ሦስት ትምህርት ቤቶችን ለማስገንባት ቃል ገብተዋል፤ በዝግጅቱም በጨረታ ብቻ 51 ሺህ 260 ዶላር ወይም 1ሚሊዮን 538 ሽህ የሚደርስ ብር ተሰብስቧል።

ከአማራ ተወላጆች እና የአማራ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ኢትዮጵያውያን ጋር የተደረጉ ምክክሮች ስኬታማ እንደሆኑ የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አስታወቁ፡

የሥራ ኃላፊዎቹ በሰሜን አሜሪካ ግዛቶች ከሕዝብ ጋር ሲያካሂዷቸው የነበሩትን ምክክሮች አስመልክተው ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና በአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ፈንታ የተመራ የአማራ ክልል የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ በሰሜን አሜሪካ-ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው፣ አትላንታ፣ ዴንቨር፣ ኮሎምበስ፣ ሚኒሶታ፣ ሳንሆዜ እና ሲያትል ከሚኖሩ የአማራ ተወላጆች እና የአማራ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ኢትዮጵዉያን ጋር ሲመክር መሰንበቱ ይታወሳል፡፡ ምክክሩ በክልላዊ እና ሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች፣ በክልሉ ልማት እና ኢንቨስትመንት ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ የአልማን የቀጣይ ሦስት ዓመታት የለውጥ ዕቅድ ዕውን ለማድረግ እና ዓላማውን በዘላቂነት ለመደገፍ የዳያስፖራው ሚና ምን መሆን እንዳለበትም በምክክሩ ትኩረት ተደርጓል፡፡ ከተሳታፊዎችም በሁሉም ዘርፎች ጥያቄ እና ምክረ ሀሳቦች ቀርበው ምክክር ተደርጎባቸዋል፡፡

አሰራርን በአሳታፊና ቅንጅታዊ መርህ መተግበር ህዝባዊ አመኔታ ይፈጥራል!

 አሰራርን በአሳታፊና ቅንጅታዊ መርህ መተግበር የተቋምን ዘላቂነት ብቻ ሳይሆን ማህበሩ የቆመለትን የህዝብ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስችላል ሲሉ የአማራ አቀፍ ልማት


Copyright © 2012  ADA, All Rights Reserved.               Designed & Developed by :Yibeltal Ferede