በራስ አቅም የመልማት ምልክት የሆነው የአማራ ልማት ማህበር እንኳን ለ2017 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ እያለ:-

Posted on : September: 10/24
Card image

በራስ አቅም የመልማት ምልክት የሆነው የአማራ ልማት ማህበር እንኳን ለ2017 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ እያለ:-

በራስ አቅም የመልማት ምልክት የሆነው የአማራ ልማት ማህበር እንኳን ለ2017 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ እያለ:- ማህበሩ ማህበረሰቡ የራሱን ማህበራዊ ችግር በራሱ አቅም በብቃት ይፈታ ዘንድ በክልሉ፣ ከክልሉ ውጭ እና በመላው ዓለም የሚገኙ ከ97 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞችን፣ ከ4.5 ሚሊየን በላይ አባላት እና የልማት ደጋፊዎችን በማስተባበር በትምህርት፣ ጤና፣ ሥራ እድል ፈጠራ፣ የኑሮ ዘይቤ ማሻሻል እና መልሶ ማቋቋም በርካታ የልማት ተግባራትን ሲፈጽም ቆይቷል ፡፡ ማህበሩ በቀጣይ አምስት ዓመታት (2017-2021)አዲስ ስትራቴጅያዊ እቅድ ያዘጋጀ ሲሆን የእቅዱ ዋና ዋና ግቦች፡-  የላቀ ማህበር መፍጠር፣ ህዝባዊ ተሳትፎና ባለቤትነትን ማሳደግ፣ የገቢ ማስገኛ ተቋማትን ማስፋፋት፣ የአጋር አካላትን በማጠናከር ሃብት ማሰባሰብ፣ ትምህርት ቤቶችን ማሻሻል፣ የጤና ስርዓት ማሻሻል፣ የወጣቶች ስራ ፈጠራ እና ቤተሰብ ተኮር የኢኮኖሚ ግንባታ እና መልሶ ማቋቋም ላይ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ፡፡ ስለሆነም ሁሉም ማህበረሰብ የልማቱ ተሳታፊና ባለቤት እንዲሆን ማህበሩ ጥሪውን እያቀረበ በድጋሜ አዲሱ ዓመት የሰላም የፍቅር እና የአንድነት እንዲሆን እንመኛለን ፡፡ መልካም አዲስ ዓመት! ሺ ሆነን እንደ አንድ ፣አንድ ሆነን እንደ ሺ ! አማራ ልማት ማህበር

Gallary


The News