የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከአልማ ጋር በመተባበር በጠለምት ወረዳ በተፈጥሮ አደጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ።

Posted on : September: 18/24
Card image

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከአልማ ጋር በመተባበር በጠለምት ወረዳ በተፈጥሮ አደጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከአልማ ጋር በመተባበር በጠለምት ወረዳ በተፈጥሮ አደጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ። -----------//////-------------- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከአልማ ጋር በመተባበር ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው አልባሳትን በጠለምት ወረዳ በተፈጥሮ አደጋ ለተፈናቀሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ አደረገ። የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) ምክትል ዋና ሥራ አሥፈጻሚ መዝገቡ አንዱዓለም እንዳሉት አልማ ከሚያከናውነው የልማት ሥራዎች ባለፈ በተፈጥሮ እና ሰው ሠራሽ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ በማሠባሠብ እያደረሰ ይገኛል። አሁንም በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ በተፈጥሮ አደጋ ለተፈናቀሉ ዜጎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የተሠባሠበ ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የተለያዩ አልባሳት ለክልሉ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን አስረክቧል። በቀጣይም ተጨማሪ ድጋፎችን በማፈላለግ ተደራሽ ያደርጋል ብለዋል። በሀገር እና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ወገኖች ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል። የአማራ ክልል አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሰርክዓዲስ አታሌ ለተደረገው ድጋፍ አመሥግነው በክልሉ በሰው ሠራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ከ589 ሺህ በላይ ተፈናቃይ መኖሩን ገልጸዋል። ለዚህ ደግሞ የክልሉ አደጋ መከላከል ከተጠባባቂ ሃብት ድጋፍ እያደረገ መኾኑን ነው የተናገሩት። ድጋፉ በቂ ባለመኾኑ በመላው ዓለም የሚኖር ማንኛውም አካል ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። አሚኮ አልማ ፡08/01/2017 ዓ.ም

Gallary


The News