‹‹ በደብተርና እስክርቢቶ ችግር ምክንያት አንድም ተማሪ ከትምህርት ገበታ ውጭ ሊሆን አይገባም፡፡ ›› ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)

Posted on : September: 30/24
Card image

‹‹ በደብተርና እስክርቢቶ ችግር ምክንያት አንድም ተማሪ ከትምህርት ገበታ ውጭ ሊሆን አይገባም፡፡ ›› ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)

‹‹ በደብተርና እስክርቢቶ ችግር ምክንያት አንድም ተማሪ ከትምህርት ገበታ ውጭ ሊሆን አይገባም፡፡ ›› ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) -----------///////----------- የአባይ ህትመትና ወረቀት ፓኬጂንግ ፋብሪካ ለአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ 4 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚገመቱ 100 ሽህ የተማሪ ደብተሮችን ድጋፍ አድርጓል፡፡ ድጋፉን ያስረከቡት የአባይ ህትመትና ወረቀት ፓኬጂንግ ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ መላሽ እንደተናገሩት፤ በክልሉ ለሚገኙ በዝቅተኛ ኢኮኖሚ ለሚኖሩ ተማሪዎች 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት 100 ሽህ ደብተር ለክልሉ ትምህርት ቢሮ አስረክበናል ብለዋል፡፡ ፋብሪካው የተቋቋመበት አንዱ አላማ የትምህርት ስርዓቱን ለመደገፍና ለማገዝ ነው ያሉት ዋና ስራ አስኪያጁ፤ እንደ ሀገር ተወዳዳሪ ለመሆን ከክልሉና ከክልሉ ውጭ የሚገኙ ተማሪዎችን ለመደገፍ ዝግጁ ነንም ነው ያሉት፡፡ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሙሉነሽ ደሴ በበኩላቸው፤ ፋብሪካው ከዚህ በፊት በክልሉ የሚገኙ ችግረኛ ተማሪዎችን በትምህርት ቁሳቁስ እያገዘ መምጣቱን ጠቁመው በዛሬው እለት ላደረገው ድጋፍም በተማሪዎቹ ስም ታላቅ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በደብተርና እስክርቢቶ ችግር ምክንያት አንድም ተማሪ ከትምህርት ገበታ ውጭ አይሆንም ሲሉ አክለው የተናገሩት ሃላፊዋ፤ በዘንድሮው ዓመት የሌሎች ድጋፎችን ሳይጨምር በቢሮ ብቻ 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ደብተሮችን ገዝተን ለችግረኛ ተማሪዎች ሰጥተናል ብለዋል፡፡ ደግነት ለራስ እንደሆነ ያብራሩት ዶክተር ሙሉነሽ ደሴ፤ ሌሎች በጎ አድራጊ ድርጅቶች፣ ተቋማት እና ግለሰቦች ለችግረኛ ተማሪዎች የበኩላችሁን እገዛና ድጋፍ እንድታደርጉ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡መረጃው የአማራ ኮሙኒኬሽን ነው፡፡ አልማ ፡20/01/2017 ዓ.ም

Gallary


The News