የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻልና ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል አልማ ፍቱን መዳህኒት ነው!!

Posted on : October: 02/20
Card image

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻልና ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል አልማ ፍቱን መዳህኒት ነው!!

ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሊያደርስ የሚችለውን ተፅዕኖ በመቆቋም የተሳካ የመማር ማስተማር ስራ ለመስራት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከአማራ ልማት ማህበር ጋር ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊና የአማራ ልማት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ም/ሰብሳቢ ገለፁ፤፤ ዶ/ር ይልቃል ከፍያለ ዛሬ ለአማራ ብዙሀን መገናኛ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በብሄራዊ ክልሉ ከ6 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቻችን ተመዝግበው ጥቅምት ዘጠኛ 16 እና 30/2013 ዓ.ም መደበኛ ትምህርታቸውን ይጀምራሉ ብለዋል፡፡ ከኮቪድ -19 ወረርሽኝን መከላከል በሚያስችል መንገድ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠል ክልላዊ ቅንጅትና ትብብር ያስፈልጋል ያሉት ዶ/ር ይልቃል ተማሪዎች ከተለመደው ውጭ ርቀታቸውን ጠብቀው በመቀመጣቸው ምክንያት በመማሪያ ክፍል በኩል ሊያጋጥም የሚችለውን ጥበት ለማስተካከል፤ በትምህርት ቤቶች ሳኒታይዘር ፤ ውሀ፤ ፈሳሽ ሳሙና ፤የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ፤የሙቀት መለኪያና የመሳሰሉ ቁሳቁሶችን ለማሟላት የክልሉ መንግስት፤ አማራ ልማት ማህበርና ቢሮው ተቀናጅተው በመስራት ላይ ናቸው ብለዋል፡፡ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻልና ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል አልማ ፍቱን መዳህኒት መሆኑን ም/የቦርድ ሰብሳቢው ገልፀዋል፡፡ መምህራን ወላጆች፤ተማሪዎችና መላ ህብረተሰቡም በገንዘብ ፤ቁሳቁስና ሙያ ልማት ማህበሩን በመደገፍ ወረርሽኙ በመማር ማስተማሩ ሂደትና በሀገር ተረካቢ ትውድ ዘንድ ወረርሽኙ ሊያደርስ የሚችለውን አደጋ መቆቋምና መከላከል ይገባልም ብለዋል፤ዶ/ር ይልቃል፡፡ በማህበሩ የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ መዝገበ አንዱአለም በበኩላቸው ልማት ማህበሩ የክልሉን የትምህርት ቤቶች ደረጃ ለማሻሻል ስትራተጅ ዕቅድ አጽድቆ በመስራት ላይ መሆኑን ጠቁመው ኮቪድ -19 ወረርሽኝ ተማሪዎች በክል ጥበት ምክንያት የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዳይደናቀፍ 6 ሺ የሚጠጉ መማሪያ ክፍሎች በዚህ አመት ብቻ ይገነባሉ ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ማህበሩ ወረርሽኙ የሚያደርሰውን አደጋ ለመከላከል ሳኒታይዘር እያመረተ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ላይ መሆኑን ጠቅሰው የአቅርቦት ዕጥረት እንዳይፈጠር የጥሬ ዕቃ እና የፈሳሽ ሳሙናም ለማምረት ማህበሩ ዝግጅት ማጠናቀቁን አቶ መዝገበ ጠቁመዋል፡፡

Gallary


The News