መመረቅ እንጅ የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ ልማዳችን አይሆንም! ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የአብክመ ርዕሰ-መስተዳደር

Posted on : October: 23/20
Card image

መመረቅ እንጅ የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ ልማዳችን አይሆንም! ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የአብክመ ርዕሰ-መስተዳደር

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አቶ ተመሥገን ጥሩነህ ይህን ያሉት ጥቅምት 8/2013 ዓ.ም በምሥራቅ ጎጃም ዞን ጎዛምን ወረዳ አልማ በ12 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ያስገነባውን የገጠር ፋና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መርቀው በከፈቱበት ወቅት ነው ፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞን ጨምሮ የክልልና የዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ፣የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡ ርዕሰ -መስተዳድሩ በምረቃው ወቅት ባስተላለፍት መልዕክት አማራ ልማት ማህበር በጎዛምን ወረዳ አዲስና ጉሊት ቀበሌ የገጠር ፋና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ሲገነባ የአካባቢውን ማህበረሰብ በማሳተፍ ነው፡፡ በተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች አልማ ሰፊ ስራ እየተሰራ ነው ፡፡ የዚህ ውጤት ደግሞ የህዝብ ተሳትፎ ነው ፡፡ ተሳትፎው ደግሞ በገንዘብ መዋጮ ብቻ ሳይሆን እውቀታቸውን እና ጉልበታቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ በማድረግ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አልማ የትምህርት ቤት ግንባታውን ለተደራጁ ወጣቶች ሰጥቶ ማስገንባቱን ገልጸው ወጣቶችም የተጣለባቸውን ሃላፊነት በብቃት በመወጣት በ4ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቀው ለምረቃ እንዲበቃ በማድረጋቸው በእጅጉ ልንኮራባቸው ይገባል ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡ በክልላችን ሁሉም ልማት ሊመጣና ሊረጋገጥ የሚችለው አርሶ አደሩ ፣የከተማው ማህበረሰብ ፣የሃይማኖት አባቶች ፣የሃገር ሽማግሌዎች ፣ባለሀብቶች ፣ሙህራን እና ወጣቶች የጋራ እርብርብ ሲያደርጉ መሆኑን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳደሩ በአሁኑ ስዓትም መመረቅ እንጅ የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ ልማዳችን አይሆንም ብለን ወደ ስራ በመግባታችን በክልላችን ብዙ የልማት ፍሬዎችን እያየን ነው ብለዋል ፡፡

Gallary


The News