አማራ ልማት ማህበር ለማህበራዊ ልማት ጎን ለጎን በአንበጣ መንጋ ለተጎዱ ወገኖች ፈጥኖ ምላሽ መስጠቱ በራስ የመተማመን ስሜት ፈጥሮልናል ሲሉ በደቡብ ወሎ አስተዳደር ዞን የወረባቦ ወረዳ ነዋሪዎች ገለፁ ፡፡

Posted on : October: 28/20
Card image

አማራ ልማት ማህበር ለማህበራዊ ልማት ጎን ለጎን በአንበጣ መንጋ ለተጎዱ ወገኖች ፈጥኖ ምላሽ መስጠቱ በራስ የመተማመን ስሜት ፈጥሮልናል ሲሉ በደቡብ ወሎ አስተዳደር ዞን የወረባቦ ወረዳ ነዋሪዎች ገለፁ ፡፡

ነዋሪወቹ ይህን የገለፁት ማህበሩ ሰብላቸው በአንበጣ ለወደመባቸው ቤተሰቦች ሚሰጥ 200 ኩንታል የፊኖ ዱቄትና 10 ሺ 743 ባለ50 ሉክ ደብተርና 10 ሺ እስክርቢቶ ቦታው ድረስ በመሄድ ባስረከበበት ወቅት ነው፡፡ ማህበሩ ድጋፉን ለህብረተሰቡ ባስረከበበት ወቅት የወረባቦ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ካሊድ መሀመድ እንዳብራሩት አልማ ህዝባዊ ተሰትፎ ለዘላቂ ልማት 2012-2014 በሚል መሪ ቃል የወረዳውን ትምህርት ቤቶች ደረጃ በማሻሻል በሚገኝበት ወቅት ይህ አይነቱ አደጋ በአካባቢያቸው ሲፈጠር ደግሞ ህብረተሰቡን ለመደገፍ ፈጥኖ ያቀረበው አልማ ምህብና የትምህርት ቁሳቁስ በማህበራችን ላይ መተማመን ስሜት ፈጥሮብኛል ብለዋል፡፡ አርሶ አደሩ ምርቱን ብቻ ሳይሆን በስነ-ልቦናም በተጎዳበት ወቅት አማራ ልማት ማህበር ያቀረበው ድጋፍ ለችግር ደራሽነቱን ብቻ ሳይሆን ወገንተኛነቱንም በተግባር ያሳየበት ነው ያሉት ደግሞ የወረባቦ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አደም አራጋው ናቸው፡፡

Gallary


The News