አማራ ልማት ማህበር የእንቦጭ አረምን ለማጥፋት የሚያገለግል የመዋኛና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ለጣና ሀይቅና ሌሎች የውሀ አካላት ጥበቃና ልማት መ/ቤት አስረከበ ፡፡

Posted on : December: 15/20
Card image

አማራ ልማት ማህበር የእንቦጭ አረምን ለማጥፋት የሚያገለግል የመዋኛና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ለጣና ሀይቅና ሌሎች የውሀ አካላት ጥበቃና ልማት መ/ቤት አስረከበ ፡፡

ድጋፉን ለጣና ሀይቅና ሌሎች የውሀ አካላት ጥበቃና ልማት መ/ቤት ርክክብ ያደረጉት የአልማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መዝገበ አንዷለም የቁሳቁስ ድጋፉ በጣና ሀይቅ ላይ የተከሰተውን እንቦጭ ለመከላከል የሚያገለግል 300 የዋና ልብስ ፤500 የእጅ ጓንት 56 ካርቶን የገላ ሳሙና በድምሩ 700 ሺ ብር በላይ የሚያወጣ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የእንቦጭ አረምን ለማጥፋት የሚያገለግለው ቁሳቁስ የተገኘው የአልማ በጎ ፈቃደኞችንና ዳያስፖራውን የተቀናጀ አቅም ወደ ልማት የማስገባትና ክልሉን የመደገፍ ፍላጎት ያላቸውን አካላት በማስተባበር ሂደት በአሜሪካ የዲሲ ፤ሜሪላንድና ቨርጅንያ የማህበሩ አባላት መሆናቸውን አቶ መዝገበ ተናግረዋል፡፡ የጣና ሀይቅና ሌሎች የውሀ አካላት ጥበቃና ልማት ተወካይ አቶ ጤናው ምንውየለት የቁሳቁስ ድጋፉን ሲረከቡ እንደገለፁት አልማ በትምህርት ጤናና ስራ እድል ፈጠራ ከሚያደርገው ድጋፍ ጎን ለጎን የክልሉ ህብረተሰብ በተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋ ሲያጋጥመው እያሳየ የሚገኘው ፈጣን ምላሽ ማህበሩ ህዝባዊነቱንና አቅሙን እያሳደገ ለመምጣቱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

Gallary


The News