በምስራቅ ጎጃም ዞን የባሶ ሊበን ወረዳ አልማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የትምህርት እና የጤናኬላ ግንባታዎችን አጠናቆ ለተጠቃሚዎች ዝግጁ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ ።

Posted on : December: 17/20
Card image

በምስራቅ ጎጃም ዞን የባሶ ሊበን ወረዳ አልማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የትምህርት እና የጤናኬላ ግንባታዎችን አጠናቆ ለተጠቃሚዎች ዝግጁ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ ።

የባሶ ሊበን ወረዳ አልማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2012 በጀት አመት ከመደበኛ አባላት ሀብት በማሰባሰብ በደን ቀበሌ በአዲስ ለሚገነባው የደን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት1ሚሊዩን 986ሺ99ብር ወጭ በማድረግ 1ብሎክ 4የመማሪያ ክፍሎችያሉት ፣ በየላም ገጅ ቀበሌ ይልማን ቦሴ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት 1ብሎክ 4የመማሪያ ክፍሎች ያሉትና የመምህራን ቢሮ የያዘ በ2ሚሊዩን 389ሺ124 ብር በመገንባባት ከጭቃክፍል ወደ ብሎኬት መቀየር መቻሉን የባሶ ሊበን ወረዳ አልማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አድምቃቸው አሳብ ተናግረዋል ፡፡ አቶ አድምቃቸው አክለውም የማህበረሰቡን ጤና ለመጠበቅ የሚያገለግል በባሶ ሊበል ወረዳ ምችግ ቀበሌ 353ሺ ብር ወጭ በማድረግ ጤና ኬላ መገንባት መቻሉን ገልጸው አማራ ልማት ማህበር በወረዳው እየሰራው ያለውን ስራ በመመልከት የህብረተሰቡ ተነሳሺነት እየጨመረ በመምጣቱ የ2013 ዕቅድን ለማሳካት ከወረዳው ህዝብና መንግስት ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ስራ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡ አልማ06/04/2013ዓ.ም

Gallary


The News