የአማራ መገናኛ ብዙሀን ለህዝብ የሚያሰራጫቸው የዜናና ፕሮግራም ዝግጅቶች ለክልሉ ማህበራዊ ልማት መነሻ ሆነው እያገለገሉ መሆኑን የአማራ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ፈንታ ገለፁ፡፡

Posted on : January: 15/21
Card image

የአማራ መገናኛ ብዙሀን ለህዝብ የሚያሰራጫቸው የዜናና ፕሮግራም ዝግጅቶች ለክልሉ ማህበራዊ ልማት መነሻ ሆነው እያገለገሉ መሆኑን የአማራ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ፈንታ ገለፁ፡፡

አቶ መላኩ ፈንታ ህዝባዊ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት አልማ 2012-2014 በሚል መነሻ ማህበሩ የሚመራበትን ስትራተጅያዊ የለውጥ ዕቅድ ለብዙሀን መገናኛ ሰራተኞች ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት ዕቅዱ የክልሉን አጠቃላይ ት/ቤቶች ደረጃ ከሚገኙበት 16 በመቶ ወደ 50 በመቶ ከፍ የማድረግ ዓላማ ቢኖረውም መነሻው የህዝብ ጥያቄና የክልሉ መገናኛ ብዙሀን በየጊዜው በዜናና ፕሮግራም ዝግጅታቸው የሚያደርጉት ጉትጎታ ነው ብለዋል፡፡ የአማራ ብዙሀን መገናኛ ስራዎችና ተቋሙ የሚመራበት የአማራ ክልል ህዝብ ማህበራዊ ለውጥ መሪ ቃል ልማት ማህበራችን ዕቅዱን ከማቀድ ጀምሮ እስከ አፈፃፀም ድረስ ወሳኝ ናቸው ያሉት አቶ መላኩ የተቋሙ ሰራተኞች የልማት ማህበሩ አባል በመሆን ፤የሙያ አስተዋፅኦ በማድረግና እንደተቋምም የፕላትንየም አባል ሆኖ አስተዋፅኦ በማበርክት በዓርያነት የሚጠቀስ ተግባር እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የውይይቱ ተሳታፊ ጋዜጠኞች በበኩላቸው አማራ ልማት ማህበር የሚያከናውነውን የማህበራዊ ልማት ተገቢነት ያለውና ሊደገፍ የሚገባው መሆኑን ጠቅሰው ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎች ት/ቤት /TALENT ACADEMY/ ወይም ሌላ በብዙሀን መገናኛ ሰራተኞች አስተዋፅኦ የሚገነባና በስማቸው የሚጠራ ልዩ ፕሮጀከት ለመፈፀም ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ የብዙሀን መገናኛ ሰራተኞች ይህን ጉዳይ በበጎ ፈቃደኝነት የሚያስፈፅምና የሚከታተል በጋዜጠኛ አብርሀም በውቀት የሚመራ አምስት አባላት የሚገኙበት ኮሚቴ በማዋቀር ወደ ተግባራዊ ስራ ግብተዋል፡፡

Gallary


The News