በጎንደርና አካባቢው የአልማ ኮርፖሬት አባላት ምክክር መድረክ ህዝባዊ ተትፎ ለዘላቂ ልማት አልማ 2012-2014 በሚል መሪ ቃል የሚመራውን የለውጥ ዕቅድ ለማሳካት በጋራም ሆነ በተናጥል የድርሻቸውን ለመወጣት እንደሚንቀሳቀሱ የጋራ ውሳኔ አሳለፉ፡፡ የኮርፖሬት አባላቱን የሚያስተባብራቸው ሰባት አባላት ያሉት ኮሚቴ አቋቁመዋል ፤ የሁለት አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ደረጃ ማሻሻያ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡

Posted on : January: 22/21
Card image

በጎንደርና አካባቢው የአልማ ኮርፖሬት አባላት ምክክር መድረክ ህዝባዊ ተትፎ ለዘላቂ ልማት አልማ 2012-2014 በሚል መሪ ቃል የሚመራውን የለውጥ ዕቅድ ለማሳካት በጋራም ሆነ በተናጥል የድርሻቸውን ለመወጣት እንደሚንቀሳቀሱ የጋራ ውሳኔ አሳለፉ፡፡ የኮርፖሬት አባላቱን የሚያስተባብራቸው ሰባት አባላት ያሉት ኮሚቴ አቋቁመዋል ፤ የሁለት አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ደረጃ ማሻሻያ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡

አማራ ልማት ማህበር ከሶስት አመታት ወዲህ ትክክለኛ የአማራ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ማፋጠኛ ህዝባዊ ማህበር መሆኑን አረጋግጠናል ያሉት የውይይቱ ተሳታፊዎች የነገ አገር ተረካቢ ወጣቶች በአዕምሮ የሚቀረፁባቸው ት/ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቁና በቁሳቁስ የተሟሉ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት በጋራም ሆነ በተናጥል ትምህር ተቋማትን በአጭር ጊዜ ውስጥ ገንብተን እናስረክባለን ብለዋል፡፡ በከተማው ውስጥ ከሚገኙና ደረጃቸውን ካላሟሉ አንጋፋ ት/ቤቶች ውስጥ አንዱ የአፀፄ ፋሲለደስ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የማሻሻያ ግንባታ ዲዛይን በጎንደር ዩኒቨርስቲ በጎ-ፈቃደኛ ምሁራን ተሰርቶ የማሻሻያ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ በክቡር ከናቲባ አቶ ሞላ መልካሙ ነክቡር አቶ መላኩ ፈንታ የአልማ ዋና አስራ አስፈፃሚና በጎንደር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር አስራት ሀረገ-ወይን ተቀምጧል፡፡ የማሻሻያ ግንባታው 12 ክፍሎች ያሉት ባለሁለት ፎቅ መማሪያ ክፍልና ባለ አንድ ፎቅ፤ ቤተ -መፃህፍት እንዲሁም ቤተ- ሙከራ በአልማ ፤በጎንደር ከተማ አስተዳደርና በዩኒቨርስቲው ትብብር አጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ በስነ-ስርዓቱ ወቅት ተገልጧል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በከተማው አራት በጎ -ፈቃደኛ ግለሰቦች በመመካከር በፈለገ-አብዮት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለ አንድ ብሎክና አምስት የመማሪያ ክፍሎች ያሉትን የትምህርት ቤት ማሻሻያ ግንባታ በቀጣይ ግንቦት ወር አጠናቀው ለማስረከብ የሚያስችል የመሰረት ድንጋይ በዕለቱ አስቀምጠዋል፡፡ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሞላ መልኬ ግንባታው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ የአመራር ክትትልና ድጋፍ እንደማይለየው ገልፀዋል፡፡

Gallary

The News