አልማ- ዩኤስ ኤይድ ቤተሰብ ተኮር ኤች አይቪ መከላከል፤ እንክብካቤና ህክምና ፕሮጀክት ደሴ ማስተባበሪያ ለአንድ ሺ አንድ መቶ ሶስት ተማሪዎችና ህፃናት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

Posted on : September: 25/21
Card image

አልማ- ዩኤስ ኤይድ ቤተሰብ ተኮር ኤች አይቪ መከላከል፤ እንክብካቤና ህክምና ፕሮጀክት ደሴ ማስተባበሪያ ለአንድ ሺ አንድ መቶ ሶስት ተማሪዎችና ህፃናት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

የአልማ ደሴና አካባቢው ማስተባበሪያ ሀላፊ አቶ አበባው ታደሰ እንደገለፁት 308 ሺ ብር ወጭ የተደረገበትንና መስከረም 12/2014 ዓ.ም የአንድ ሴሚሰተር ደብተርና እስክርፒቶ የተደገፉት አንድ ሺ አንድ መቶ ሶስት ህፃናት ተማሪዎችም ሆኑ ቤተሰቦቻቸው ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ መሆናቸውን ፕሮጀክቱ አረጋግጧል ብለዋል፡፡ የድጋፉ ተጠቃሚዎች በደሴ፤ ቃሉ፤ ከምሴና ባቲ ከተማ የተመረጡ ናቸው ያሉት በደሴና አካባቢው የአልማ -ዩኤስ አይድ ቤተሰብ ተኮር ኤች አይቪ መከላከል፤ እንክብካቤና ህክምና ፕሮጀክት የኦቪሲ አገልግሎት ስፔሻሊስት አቶ መስፍን ሰሎሞን ናቸው፡፡

Gallary

The News