አማራ ልማት ማህበር በጎ-ፈቃደኛ ኢትዮጲያውያንና ትውልደ ኢትዮጲያዊያን በማስተባበር በትግራይ ወራሪ ሀይል ጉዳት ለደረሰባቸው ጭና እና አካባቢው ነዋሪዎች የእርቢ በጎችን በስጦታ አበረከተ፡፡

Posted on : January: 24/22
Card image

አማራ ልማት ማህበር በጎ-ፈቃደኛ ኢትዮጲያውያንና ትውልደ ኢትዮጲያዊያን በማስተባበር በትግራይ ወራሪ ሀይል ጉዳት ለደረሰባቸው ጭና እና አካባቢው ነዋሪዎች የእርቢ በጎችን በስጦታ አበረከተ፡፡

አማራ ልማት ማህበር ለጭና እና አካባቢው የጦርነት ተጎጅዎች የዕርቢ በጎችን በስጦታ እንዲበረከትላቸው ያደረገው ነዋሪነታቸው በአሜሪካን ሀገር ኒውዮርክ ክፍለግዛት የሆኑትን አቶ ታምራት ሰይፈያሬድ እና ጓደኞቹ በበጎ ፈቃደኝነት ያሰባሰቡትን አንድ መቶ ሺ ብር (100 000.00) ቦታው ድረስ ተጉዘው የደረሰውን ችግር እንዲመለከቱ በማድረግ ነው፡፡ በአቶ ታምራትና ጓደኞቹ ድጋፍ በተገኘ አንድ መቶ ሺ ብር ወጭ የተገዙትን የዕርቢ በጎች ለተጎጅዎች የተከፋፈሉበት መስፍርት በተመለከተ በወራሪው የትግራይ ሀይል በከፈተው ጦርነት የቤተሰቦቻቸውን አባል በሞት ፤ ቤት ንብረታቸውን በዘረፋና ቃጠሎ ምክንያት የጉዳቱ ተጠቂዎች መካከል በቁጥር ሀምሳ (50) ያህሉ ከዚህ በፊት ድጋፉ ሳይደርሳቸው የቀሩና ወረፋ ይጠባበቁ የነበሩ መሆናቸውን የቀበሌው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሞላልኝ አባይ ገልፀዋል፡፡ የእናት በጎች ለተጠቃሚዎች በተከፋፈሉበት መድረክ ንግግር ያደረጉት የዳባት ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ በውጭ የሚኖሩ ወገኖቻችን ወራሪው ያደረሰውን ጉዳት ሰምተው ሀብት በማሰባሰብ ቀበሌያችን ድረስ በመምጣት ያደረጉት የቁሳቁስና የሞራል ድጋፍ ተጎጅዎችን እጅግ ያስደሰተና አለኝታነታቸውንም ያስመሰከረ ነው ብለዋል፡፡ የድጋፍ ሀብቱን ከአሜሪካን ሀገር ድረስ በማምጣት ለተጎጅዎች ያስረከቡት አቶ ታምራት በበኩላቸው የእርቢ በጎች ድጋፍ ተጎጅዎች በዘላቂነት ለማቋቋም ካላቸው ፍላጎት የመነጨ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይም ከዚህ በተሸለ መንገድ ወራሪው ሀይል በክልሉያደረሰውን ጉዳት መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ሂደት ንቁ ተሳታፊ እንደሚሆኑ ገልፀዋል፡፡ በአማራ ልማት ማህበር የማዕከላዊ ጎንደርና አካባቢው አስተባባሪ አቶ አለኋኝ ጓዴ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጲያዊያንና ትውልደ ኢትዮጲያዊያን በዘላቂ ልማት ከፍተኛ አበርክቶ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አውስተው አሁንም ክልሉ በወራሪ ሀይል በተጠቃበት ወቅት በዕለት ደራሽና መልሶ ግናባታ እያደረጉ ለሚገኙት አስተዋፅኦ በተጠቃሚው ህዝብ ስም የላቀ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በእርቢ በጎች ርክክብ ስነ ስርዓት የተገኙ የዳባትና አካባቢው አገር ሽማግሌዎች እንደገለፁት ድጋፉ ወራሪውን ሀይል በመመከት ሂደት የልጆቻቸውንና የቤተሰብ ሀላፊ አባዎራ ጭምር ያጡ ቤተሰቦች በወረዳው ስላሉ ከአንድ ቀበሌ ባሻገር ሁሉንም የጦርነቱ ተጠቂዎች የሚሸፍንበት ሁኔታ ቢመቻች ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

Gallary


The News